All Mezmur / ሁሉን መዝሙር
እግዚአብሔርን አመስግኑት
Listen / ያድምጡ
Lyrics / ግጥም
እግዚአብሔርን አመስግኑት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት (2) ሰማይን ያለ ምሰሶ ምድርንም ያለ መሠረት ያጸናው እርሱ ነው ሥራህ ድንቅ ነው በሉት አዝ የባሕርንም ጥልቀት የመጠነ ዳርቻዋን የወሰነ እግዚአብሔርን አመስግነት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት አዝ ማዕበል ነፋስ የሚገሥጽ ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት አዝ ንጹሐ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ የነገሥታት ንጉሥ አልፋና ዖሜጋ ዘለዓለም እርሱ የማይለወጥ እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት አዝ ጥበብን የሚገልጽ ጥበበኛ ፍርድ የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም እግዚአብሔር ግሩም ነው ዘለዓለም ዝመሬ